top of page

ጥቅምት 21፣2017 - በብሔራዊ ቤተ መንግስት ሲጠበቅ የነበረ 400 ኪሎ ግራም ወርቅ ለብሔራዊ ባንክ መሰጠቱ ተሰማ

  • sheger1021fm
  • Oct 31, 2024
  • 1 min read

በብሔራዊ ቤተ መንግስት ሲጠበቅ የነበረ 400 ኪሎ ግራም የሚመዝን ወርቅ ለብሔራዊ ባንክ መሰጠቱ ተሰማ፡፡


በብሔራዊ ቤተ መንግስት የተገኘው 400 ኪሎ ግራም #ወርቅ ተቆልፎበት የተቀመጠ እንደሆነና ብሔራዊ ባንክ ጭምር የማያውቀው እንደሆነ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ለእንደራሴዎች ምክር ቤት ባደረጉት ንግግር ጠቅሰዋል፡፡


ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ 400 ኪ.ግ ወርቅ ከተቆለፈበት መገኘቱን ያረጋገጡት የቀድሞው ኢዩቤልዩ፣ የአሁኑ #ብሔራዊ_ቤተ_መንግስት መታደሱን በገለፁበት ወቅት ነው፡፡


የብሔራዊ ቤተ መንግስት አሁን ባይታደስ ለፈረሳ ተቃርቦ እንደነበር የተናገሩት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ለዚሁም ከዚህ በፊት የነበሩት መሪዎች የ #ፊውዳል ቤት በሚል እሳቤ ለመመልከት ባለመፈለጋቸው እንደሆነ አስታውሰዋል፡፡


እሸቴ አሰፋ

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page