በኢትዮጵያ የተፈቀደው ፍራንኮ ቫሉታ ዳግም ሊከለከል እንደሚችል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ፍንጭ ሰጡ፡፡
#ፍራንኮ_ቫሉታ የተፈቀደው ከዚህ ቀደም በህገ-ወጥ መንገድ ከሀገር የሸሸ ሀብት የሚመለስበትን እድል መስጠት አንዱ ምክንያት እንደነበር ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጠቅሰዋል፡፡
እንዲሁም የውጭ ምንዛሪ ዋጋ በገበያው እንዲመራ መወሰኑን ተከትሎ ለባንኮች አዲስ ልምምድ ስለነበር #የገቢ_ምርት ላይም ችግር እንዳያጋጥም ታልሞ ፍራንኮ ቫሉታ መፈቀዱን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተናግረዋል፡፡
በህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት ተገኝተው ከምክር ቤት አባላት ለቀረቡ የተለያዩ ጥያቄዎች ምላሽ የሰጡት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ፍራንኮ ቫሉታን ምክንያት አድርገው ከሀገር ሀብት የሚያሸሹ መኖራቸውን አብራርተዋል፡፡
በመሆኑም በውሳኔው ላይ የማስተካከያ እርምጃ በቅርቡ ሊወሰድ እንደሚችል በንግግራቸው ፍንጭ ሰጥተዋል፡፡