የኦሮሚያ ኅብረት ሥራ ባንክ ከ200 በላይ "ስማር" ሲል የጠራቸውን ቅርንጫፎችን በተለያዩ አካባቢዎች መከፈቱን ተናገረ።
ይህም የባንኩ ደንበኞች ከወረቀት ንከኪ ነፃ በሆነ መንገድ ለዚህ አገልግሎት የተዘጋጁ ታብሌቶችን በመጠቀም ብቻ የባንክ አገልግሎት ማግኘት የሚያስችል ነው ተብሎለታል።
በዚህም እንደ ገንዘብ ማስገባት፣ ማውጣትና ማስተላለፍ ያሉ አገልግሎቶችን ደንበኞች ዲጂታል በሆነ መንገድ ማግኘት የሚችሉበትን አሠራር ተዘርግቷል ተብሏል።
ባንኩ "ስማርት" ሲል በጠራቸው የባንክ ቅርንጫፎቹ ዘመናዊ የአገልግሎት አሰጣት፣ የሥራ ብቃትን መጨመር ብቻ ሳይሆን ባንኩ የደንበኞቹን ፍላጎት በቀላሉ ለማሟላት የሚያስችል፣ ባንኩን ምቹና ተመራጭ የሚየደርግ ነው ብሏል።
#የኦሮሚያ_ሕብረት_ሥራ_ባንክ ከ200 በላይ "ስማር" ሲል የጠራቸውን ቅርንጫፎችን መከፈቱን ባበሰረበት ሥነ - ሥርዓት ላይ የባንኩ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ደርቤ አስፋው እንዲሁም የብሔራዊ ባንክ ምክትል ገዥ አቶ ሰለሞን ደስታና ሌሎች እንግዶች ተገኝተዋል።
ከ13 ሚሊዮን በላይ ደንበኞች አሉኝ ያለው የኦሮሚያ ሕብረት ስራ ባንክ የዲጂታል አገልግሎቱን ለማሳደግና በዲጂታል ፈጠራ ልቆ ለመገኘት በርካታ በፈጠራ የታገዙ አገልግሎቶችን ለደንበኞቹ በማቅረብ ላይ እንደሚገኝ ተናግሯል።
ንጋቱ ሙሉ
コメント