top of page

ጥቅምት 22፣2017 - በአዲስ አበባ ቦሌ ክ/ከተማ በተለምዶ ማሪያም ማዞሪያ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ የእሳት አደጋ በቤቶች ላይ ጉዳት አደረሰ

  • sheger1021fm
  • Nov 1, 2024
  • 1 min read

በአዲስ አበባ ከተማ ቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 12 በተለምዶ ማሪያም ማዞሪያ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ፤ ዛሬ ከ6፡38 ገደማ ያጋጠመ የእሳት አደጋ በመኖሪያ ቤቶች ላይ ጉዳት አደረሰ፡፡


በአዲስ አበባ እሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነት ባለሞያ አቶ ንጋቱ ማሞ ለጊዜው ቁጥራቸው ያልተለየ ተጠጋግተው የተሰሩ የቆርቆሮ ቤቶች ተቃጥለዋል ብለዋል፡፡


አደጋውን ለመከላከል ከ70 በላይ የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች፣ 12 የአደጋ መቆጣጠር መኪኖችን 2 ቦቴ መኪኖችን ተጠቅመዋል ተብሏል፡፡


የተያዘው ጥቅምት ወር ደረቅና ነፋሻማ በመሆኑ የእሳት አደጋን ያባብሳል ጥንቃቄ ሊደረግም ይገባል ሲሉ አቶ ንጋቱ ማሞ አሳስበዋል፡፡


ወንድሙ ሀይሉ

コメント


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page