#ሳውድ አረቢያ
በሳውድአረቢያ ለጋዛ ተፈናቃይ ፍልስጤማውያን መደገፊያ የገንዘብ እርዳታ ማሰባሰብ ተጀመረ፡፡
ንጉስሳልማን እና አልጋ ወራሽ ሞሐመድ ቢን ሳልማን የእርዳታ ማሰባሰቡ ዋነኞቹ አቀላጣፊዎች እንደሆኑ አረብ ኒውስ ፅፏል፡፡
ንጉሱእና አልጋ ወራሹ ለዚሁ ዓላማ 80 ሚሊዮን የሳውዲ ሪያል መለገሳቸው ታውቋል፡፡
የሳውዲአረቢያ የሞስሊም ምሁራን መማክርት ሸንጎ ዋና ፀሐፊ ዜጎች በእርዳታ ማሰባሰቡ በስፋት እንዲካፈሉ ጥሪ አቅርበዋል ተብሏል፡፡
ከወዲሁምየሳውዲ ዜጎች እርዳታ እየለገሱ መሆኑ ታውቋል፡፡
ሳውዲአረቢያ እስራኤል የጋዛ ጥቃቷን እንድታቆም ከሚጠይቁት አገሮች አንዷ እንደሆነች ዘገባው አስታውሷል፡፡
የእስራኤልጦር የጋዛ ከተማን በሙሉ ከበባዬ ውስጥ አስገብቻታለሁ አለ፡፡
ጦሩበሐማስ ጠቅላይ መምሪያ ፣ በማዘዣ ጣቢያዎቹ እና በሮኬት ማስወንጨፊያ መሰረተ ልማቶቹ ላይ ድብደባ እየፈፀምኩ ነው ማለቱን ቢቢሲ ፅፏል፡፡
ሐማስበእስራኤል ላይ ድንገት ደራሽ ጥቃት ካደረሰ ወዲህ ለወር ያህል ጊዜ እስራኤል ጋዛን ያለ እረፍት በአየር እየደበደበችው ነው፡፡
የእስራኤልየአየር ጥቃት በሰላማዊ ፍልስጤማዊያን ላይ ሳይቀር ከፍተኛ እልቂት እያስከተለ ነው ይባላል፡፡
የጋዛየጤና ሹሞች እንዳሉት እስካሁን በእስራኤል ድብደባ የተገደሉት ፍልስጤማዊያን ብዛት ከ9,000 በልጧል፡፡
የሰላማዊፍልስጤማዊያንን ሞት ስቃይ እና መከራ ለመቀነስ ከየአቅጣጫው የተኩስ አቁም ጥሪ እየቀረበ ቢሆንም እስራኤል ግን ይሄንን አልሰማም እያለች ነው፡፡
የአሜሪካየህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለእስራኤል የጦር ወቅት መደገፊያ የ14.3 ቢሊዮን ዶላር ለማቅረብ የሚያስችለውን ህግ ማፅደቁ ተሰማ፡፡
ፕሬዘዳንትጆ ባይደን በህጉ ላይ ፊርማቸውን ማኖራቸው አጠራጥሯል፡፡
ባይደንቀደም ሲል ለዩክሬይን የጦር ወቅት መደገፊያ እና ለሌሎችም ጸጥታ ነክ ተግባራት ማከናወኛ አብረው የ106 ቢሊዮን ዶላር ጥያቄ አቅርበው እንደነበር አኒ ኒውስ አስታውሷል፡፡
የህዝብተወካዮቹ ምክር ቤት ሪፖብሊካኞች ለእስራኤል የታቀደውን መደገፊያ ብቻ ነጥለው ማፅደቃቸው ታውቋል፡፡
ጉዳዩዴሞክራቶችን ከሪፖብሊካውያኑ ጋር እያነታረከ ነው::
የህዝብተወካዮቹ ምክር ቤት አብዛኞቹ እንደራሴዎች ሪፖብሊካውያን እንደሆኑ ዘገባው አስታውሷል፡፡
ጉዳዩበብዙ ማነጋገሩ እንደማይቀር ተገምቷል፡፡
የኔነህከበደ
የሸገርንወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ… https://bit.ly/33KMCqz
Comments