top of page

ጥቅምት 23፣2016 - የቻይና መንግስት ለአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የድህረ ምረቃ የትምህርት እድል ልሰጥ ነው አለ

የድህረ ምረቃ እድል ስምምነቱን አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ እና በኢትዮጵያ የቻይና ኤምባሲ ተፈራርሟል።


የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶክተር ሳሙኤል ክፍሌ የድህረ ምረቃ የትምህርት እድል ዩኒቨርሲቲው መምህራንን እንዲያበቃ ያግዘዋል ብለዋል።


አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የራስ ገዝነት ስራ መጀመሩን ያነሱት ፕሬዝዳንቱ የተደረሰው ስምምነት ብቁ አመራሮች ለማፍራት ትልቅ እድል እንደሚፈጥር ተናግረዋል፡፡


በኢትዮጵያ የቻይና አምባሳደር ዣ ሺዋን ዩኒቨርሲቲው ከሌሎች የቻይና ዩኒቨርሲቲዎች ጋር እህትማማች ግንኙነት ያደርጋል ብለዋል።


አሁን የተፈረመው የትምህርት እድል ዩኒቨርሲቲው እራሱን እንዲያበቃ ያግዘዋል ሲሉ ተናግረዋል።


በኢትዮጵያ ያለው የቻይና ኤምባሲ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲን እንደሚደግፍ የተናገሩት አምባሳደሩ ዩኒቨርሲቲው በኢትዮጵያ ብቃት ያላቸው ተማሪዎች ለማፍራት እየሰራ ነው ብለዋል።


አሁን የተደረሰው ስምምነት ከዚህ ዓመት ጀምሮ ወደ ስራ ይገባል ተብሏል።


የቻይና መንግስት በኢትዮጵያ የትምህርቱ ዘርፍ እንዲጎለብት የተለያዩ ድጋፎች እያደረገ መሆኑን ሰምተናል፡፡


በረከት አካሉ

የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ… https://bit.ly/33KMCqz

Comments


bottom of page