top of page

ጥቅምት 26፣2017 - የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለልማት ድርጅቶች አበድሮ ያልሰበሰበው ከ845.3 ቢሊዮን ብር በላይ ነው ተባለ

  • sheger1021fm
  • Nov 5, 2024
  • 1 min read

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለመንግስት የልማት ድርጅቶች አበድሮ ያልሰበሰበው የገንዘብ መጠን ከ845.3 ቢሊዮን ብር በላይ ነው ተባለ፡፡


ይህ የተባለው ለህዝብ እንደራሴዎች ምክር መደበኛ ስብሰባው ላይ የመንግስት እዳ ሰነድ የተሰኘ ረቂቅ በቀረበበት ወቅት ነው፡፡


ለዚህም የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ያለበትን እዳ መክፈያና ካፒታሉን ለማሳደጊያ የሚውል የ900 ቢሊዮን ብር ያለው ቦንድ ለሽያጭ ሊቀርብ መሆኑን ተናግሯል፡፡

የመንግስት የልማት ድርጅቶች ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የተበደሩ ገንዘብ ለሜጋ ፕሮጀክቶች ግንባታ መሆኑ ተነግሯል፡፡


ከመንግስት የልማት ድርጅቶች ውስጥ የኢትዮጵያ መብራት ሀይል ኮርፖሬሽን አንዱ ሲሆን 191.79 ቢሊዮን ብር ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የተበደረው እዳ እንዳለበት ተነግሯል፡፡


የምድር ባቡር ደግሞ ያልመለሰው 80 ቢሊየን ብር እዳ እንዳለበት ሰምተናል፡፡


ሌላው ከፍተኛ እዳ ያለበት የኢትዮጵያ ስኳር ኮርፖሬሽን ነው የተባለ ሲሆን ከ110 ቢሊዮን ብር በላይ ተበድሮ ያልከፈው እዳ አለበት ተብሏል፡፡


ያሬድ እንዳሻው


Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page