top of page

ጥቅምት 26፣2017 - የኤች አይ ቪ ህክምናና የመከላከል ስራ ለመደገፍና ተጋላጭ የሆኑ ሰዎችን ተጠቃሚ ያደርጋል የተባለ ፕሮጀክት ዛሬ ይፋ ሆነ

በኢትዮጵያ የኤች አይ ቪ(HIV) ህክምናና የመከላከል ስራ ለመደገፍና፤ በተለይ ተጋላጭ የሆኑ ሰዎችን በመለየት ተጠቃሚ ያደርጋል የተባለ ፕሮጀክት ዛሬ ይፋ ሆነ፡፡


ፕሮጀክቱ በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኤምባሲ ፔፕፋር ኢትዮጵያ የሚደግፍ ሲሆን ጣምራ በተባለ እና በኤች አይ ቪ ላይ የሚሰራ ሀገር በቀል ድርጅትና በሌሎች 13 ማበራት በተለያዩ ክልሎች የሚተገበር ነው ተብሏል።


ማህበረሰብን በማሳተፍ ኤች አይ ቪ ኤድስን ለመከላከል የሚተገበረው ፕሮጀክት እየቀዘቀዘ የመጣውን የኤች አይ ቪ መከላከል ስራ በተለይ ወጣቶች ላይ ትኩረት አድርጎ የሚሰራ ነው፡፡


በሀገሪቱ ባለፉት ዓመታት በተከወኑ ስራዎች የኤች አይ ቪ ኤድስ ስርጭት ባለበት ቢሆንም አሁንም ግን በዓመት በበሽታው የሚያዙ ሰዎች ቁጥር ቀላል አለመሆኑ ተጠቅሷል፡፡


ኤች አይቪን ለመከላከል የሚከወኑ ስራዎችን የጸረ ኤች አይ ቪ መድኃኒት አቅርቦትና ሌሎች የምክር እና ምርመራ አገልግሎት አሰጣጦችን በተለያየ መልኩ ፕሮጀክቱ እንደሚደግፍ ተነግሯል።

በተለይ ለኤች አይ ቪ በእጅጉ ተጋላጭ ወጣቶችን በማስተማርና ግንዛቤ በመፍጠር እንዲሁም አገልግሎት የሚሰጡ የህክምና ባለሙያዎችንም መደገፍ ላይ እንደሚሰራ ሰምተናል።


በኢትዮጵያ ከዚህ ቀደም በኤች አይ ቪ ላይ የተከወኑ የመከላከልና የህክምና ስራዎች መቀነሳቸውን በጤና ሚኒስቴር የኤች አይ ቪ ቫይራል ሄፒታይስ እና የአባላዘር በሽታዎች መከላከል መሪ ስራ አስፈጻሚ አቶ ፈቃዱ ያደታ ናግረዋል።


ይህም የፈጠረው መዘናጋት አዲስ በኤች አይ ቪ የሚያዙ ሰዎችም ቁጥር እንዳይጨምረውና የመከላከል ስራው ላይ ተጽእኖ እንዳይፈጥር ስጋት መሆኑንም አቶ ፍቃዱ ጠቅሰዋል፡፡


በኢትዮጵያ 600,000 ያህል ሰዎች ኤች አይ ቪ በደማቸው እንዳለባቸውና በምርመራ ቫይረሱ ከሚገኝባቸው ሰዎች ውስጥ በተለይ ወጣቶች አብዛኛውን ድርሻ እንደሚወስዱ ሰምተናል።


ምህረት ስዩም

Comentarios


bottom of page