top of page

ጥቅምት 28፣ 2015-በላቲን አሜሪካዋ አገር ፔሩ በሺህዎች የሚቆጠሩ የተቃውሞ ሰልፈኞች ከፖሊስ ጋር መጋጨታቸው ተሰማ

  • sheger1021fm
  • Nov 8, 2022
  • 1 min read


ጥቅምት 28፣ 2015


በላቲን አሜሪካዋ አገር ፔሩ በሺህዎች የሚቆጠሩ የተቃውሞ ሰልፈኞች ከፖሊስ ጋር መጋጨታቸው ተሰማ፡፡


የተቃውሞ ሰልፈኞቹ አደባባይ የወጡት ፕሬዝዳንት ፔድሮ ካስቲሎ ስልጣን እንዲለቁ ለመጠየቅ እንደሆነ ዩሮ ኒውስ ፅፏል፡፡


ፕሬዝዳንት ካስቲሎ ምዝበራ ፈፅመዋል ተብለው እየተዋከቡ መሆኑ በዘገባው ተጠቅሷል፡፡


ካስቲሎ ወደ ፕሬዝዳንቱ ሲመጡ በሐብታሞች እና በድሆች መካከል ያለውን የኑሮ ልዩነት ለማጥበብ ቃል በመግባት ነበር ተብሏል፡፡


በአሁኑ ወቅት በፔሩ የደህንነት ምጣኔው በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ መምጣቱ ይነገራል፡፡


ፕሬዝዳንቱም ስልጣን እንዲለቁ ሕዝባዊ ጫናው እንደበረታባቸው ዘገባው አስታውሷል፡፡


የኔነህ ከበደ


Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page