top of page

ጥቅምት 28፣ 2015-በዩክሬይኗ ርዕሰ ከተማ ኪየቭ ከንቲባ ቪታሊ ክሊችኮ ነዋሪዎች ከተማዋን ለቀው ለመውጣት መዘጋጀት ይኖርባቸዋል አሉ

  • sheger1021fm
  • Nov 8, 2022
  • 1 min read


ጥቅምት 28፣ 2015


በዩክሬይኗ ርዕሰ ከተማ ኪየቭ ከንቲባ ቪታሊ ክሊችኮ ነዋሪዎች ከተማዋን ለቀው ለመውጣት መዘጋጀት ይኖርባቸዋል አሉ፡፡


በጦርነቱ ምክንያት ኪየቭ የኤሌክትሪክ አቅርቦቷን ሙሉ በሙሉ ልታጣ እንደምትችል መሰጋቱ የከንቲባው ማስጠንቀቂያ ምክንያት እንደሆነ የጀርመን ድምፅ በድረ ገፁ ፅፏል፡፡


የሰሜናዊ ንፍቀ ክበብ ክረምት ደግሞ ያለ ቤት ማሞቂያ የሚቻል አይደለም፡፡


እስካሁን ጦርነቱ በኤሌክትሪክ መሰረተ ልማቶች ላይ ባስከተለው ጉዳት ዩክሬይን ከ40 በመቶ የማያንሰውን የኤሌክትሪክ አቅርቦቷን አጥታለች ተብሏል፡፡


ከኤሌክትሪክ በተጨማሪ የኪየቭ የውሃ አገልግሎት መስተጓጎል ከጀመረ መሰንበቱ በዘገባው ተጠቅሷል፡፡


በእነዚህና ተያያዥ ምክንያች የከተማዋ ከንቲባ ነዋሪዎች ኪየቭን ለቀው ለመውጣት እንዲዘጋጁ ተናግረዋል፡፡


በኪየቭ በአሁኑ ወቅት 3 ሚሊዮን ነዋሪዎች እና በብዙ ሺህዎች የሚቆጠሩ የአገር ውስጥ ተፈናቃዮች እንዳሉ በዘገባው ተመልክቷል፡፡


የኔነህ ከበደ


Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page