top of page

ጥቅምት 28፣ 20153 ግዙፍ የሲሚንቶ አምራች ኩባንያዎች ወደ ኢትዮጵያ ገብተው ለመስራት ፍላጎት አላቸው ተባለ

  • sheger1021fm
  • Nov 8, 2022
  • 1 min read

ጥቅምት 28፣ 2015


3 ግዙፍ የሲሚንቶ አምራች ኩባንያዎች ወደ ኢትዮጵያ ገብተው ለመስራት ፍላጎት አላቸው ተባለ፡፡


ኢትዮጵያ የማዕድን ሐብቶቿን አውቃ ያወቀችውንም እንድትጠቀመው ያግዛሉ፣ ይረዳሉ የተባሉ ከ90 በላይ የውጪ ኩባንያዎች በማዕድን ኤክስፖ ላይ ለመሳተፍ ወደ ኢትዮጵያ ይመጣሉ ተብሏል፡


ወሬው የተሰማው የማዕድን ሚኒስትር ሚኒስትሩ ታከለ ኡማ ዛሬ መስሪያ ቤታቸው ያዘጋጀውን የማዕድን ኤክስፖ በተመለከተ ለጋዜጠኞች መግለጫ በሰጡበት ጊዜ ነው፡፡


ሚኒስትሩ ኢትዮጵያ ያላትን ሀብት አውቃ ወደ ምርት ለመቀየር ኤክስፖ አስፈላጊ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡


የውጪ ኩባንያዎች አገር ቤት ያለውን ማዕድን አውቀው ወደ ስራ እንዲገቡና ለሚያነሱትም የፖሊሲና ሌሎች ጉዳዮች ምላሽ ይብራራላችዋል ተብሏል፡፡


ወርቅ፣ ብረት፣ ከሰል እና ሌሎችም የተፈጥሮ ሀብቶች አምርቶ በአገር ቤት ለመጠቀም የተረፈውንም ወደ ውጪ ለመላክ በብርቱ እየተሰራ እንደሆነ ሰምተናል፡፡


ኢትዮጵያ በዓመት በቢሊየን ዶላር ብረት ለማስገባት ታወጣለች ያሉት የማዕድን ሚኒስትሩ ይህንን ለማስቀረት እና ብረትን አገር ቤት ለማምረት ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ስራ ላይ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡


ተህቦ ንጉሴ


Kommentare


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page