በኢትዮጵያ በግዙፍ ፕሮጀክቶች ስራ ከተሰማሩ የውጪ ተቋራጮች ብዙ ልምድ እየተወሰደ አይደለም ተባለ
ጉዳዩንበህግ ማዕቀፍ መምራት እንደሚያስፈልግ ታምኖበት ይኸው እየተከወነ መሆኑ ተጠቅሷል ።
ጥራትባለው የመሠረት ልማት ኢንቨስትመንት ዙሪያ ትኩረቱን ያደረገ የ2 ቀናት አውደ ጥናት ዛሬ በስካይ ላይት ሆቴል ተጀምሯል ።
የከተማናመሠረተ ልማት ሚኒስቴር ከአለም ባንክ ጋር በመተባበር ባዘጋጀው በዚሁ መድረክ ላይ ሲነገር እንደሰማነው በኢትዮጵያ አብዛኞቹ ግዙፍ ወይም ሜጋ ፕሮጀክቶች እየተሰሩ ያሉት በውጪ ተቋራጮች ነው ።
ከእነዚህየውጪ ተቋራጮች ማስቀረት የተቻለው ዕውቀት ግን እዚህ ግባ የሚባል እንዳልሆነ የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስትር ድኤታ ወንድሙ ሴታ ተናግረዋል ።
ጉዳዩንበህግ ማዕቀፍ መምራት አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ይኸው እየተሰራ ነውም ብለዋል ።
የከተማናመሠረተ ልማት ሚኒስትር ጫልቱ ሣኒ በበኩላቸው በግንባታው ዘርፍ እየታዩ ያሉ የተለያዩ ችግሮች ደካማ መሠረተ ልማት እንዲኖር ምክንያት እየሆነ እንደሚገኝ አመልክተዋል ።
ኢትዮጵያበዘርፉ ያሉ ችግሮችን በደንብ ለይታ የማስተካከያ እርምጃዎች እንድትወስድ ምክር አዘል አስተያየት የሰጡት ደግሞ በኢትዮጵያ የዓለም ባንክ ተወካይ ኦስማኔ ዲኦኔ ናቸው ።
ለዚህየዓለም ባንክ አስፈላጊውን ድጋፍ ያደርጋል ብለዋል ።
ባንኩበኢትዮጵያ የተካሄዱ የመሠረተ ልማት ስራዎችን ከዚህ ቀደምም በገንዘብ ሲደግፍ መቆየቱ ተነግሯል
ንጋቱ ረጋሣ
የሸገርንወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ… https://bit.ly/33KMCqz
Comments