የዳታ ማዕከላትን በማጠናከር ለኢትዮጵያ ለፋይናንስ ሴክተርና ለቴክኖሎጂ እድገት ለማዋል ያለመ የውይይት መድረክ በዛሬው እለት ተካሂዷል።
በመድረኩ የተገኙት የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በለጠ ሞላ ኢትዮጵያ የዲጂታል ኢኮኖሚ ሽግግሩን የሚያግዙ የተለያዩ የዳታ ማዕከላትን ወደ ስራ አስገብታለች ብለዋል።
በምሳሌነትም ዊንጉ አፍሪካ የተሰኘ የግል ዘርፍ በማሳተፍ በአይሲቲ ፓርክ ውስጥ ኢንቨስት ማድረጉን አንስተዋል፡፡
ወደ ኢትዮጵያ ገብቶ በዘርፉ ስራ ጀመረ የተባለው ዊንጉ አፍሪካ በኢትዮጵያ ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ተሾመ ወርቁ የዲጂታል ኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ለማገዝና ሀገሪቱ በቀጣናው ያላትን የዲጂታል ቅንጅትን ለማጠናከር ስራዎች እየተሰራ ነው ብለዋል።
ዊንጉ አፍሪካ ወደ ኢትዮጵያ ከገባ 18 ወራትን ማስቆጠሩን ሰምተናል።
ፍቅሩ አምባቸው
የሸገርንወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ… https://bit.ly/33KMCqz
Comments