top of page

ጥቅምት 28፣ 2017 - ''ወጣት ስራ ፈጣሪዎች ቆሻሻን ወደ ሀብትነት በመቀየር የገቢ ምንጭ እያደረጉት ነው''

ስራ ፈጣሪዎች ቆሻሻን እየለቀሙ የተፈጥሮ ማዳበሪያ፣ የተለያዩ አልባሳት፣ የመዋቢያ እቃዎች እና ሌሎችም ምርቶች እያመረቱ የገቢ ምንጭ ሲያደርጓቸው ይታያል፡፡


በሌላ በኩል #ቆሻሻ ያለ አግባብ ከተወገደ አካባቢን ይበክላል ለሰው ህይወት መጥፋት እና ህመም አንዱ ምክንያት ይሆናል፡፡


ሪች ፎር ቼንጅ ከኖርዲክ ኤምባሲዎች ማለትም ከስውዲን፣ ኖርዌይ፣ ፊንላንድ እና ዴንማርክ ኤምባሲዎች ጋር በመሆን በዘላቂነት አካባቢን ንፁህ የማድረግን የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ አዲስ አበባ ላይ አካሂደዋል፡፡


የሪች ፎር ቼንጅ የኢትዮጵያ ዋና ማናጀር መቅድም ጉልላት አሁን ላይ ወጣት ስራ ፈጣሪዎች ቆሻሻን ወደ ሀብትነት በመቀየር የገቢ ምንጭ እያደረጉት ነው ብለዋል፡፡


ሪች ፎር ቼንጅ ለ3 ዓመት የሚቆይ #ፕሮጀክት ካስጀመረ 4 ወራት እንደሞላው ያስታወሷት ማናጀሯ የፕሮጀክቱ ዋነኛ ዓላማ ቆሻሻን ላይ የስራ ፈጠራ ያላቸው ሰዎችን ለማገዝ ነው ሲሉ ያስረዳሉ፡፡


አሁን ወደ ስራ የገቡት የፈጠራ ስራዎች 1 ዓመት ሲሞላቸው በአካባቢው ላይ ምን ለውጥ አመጡ? የሚለው ጥናት እንደሚደረግ ነግረውናል፡፡


የአዲስ አበባ ከተማ #ፅዳት_አስተዳደር_ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ዶክተር እሸቱ ለማ አዲስ አበባ ውስጥ ፍሳሽ ቆሻሻ አወጋገድ ላይ ችግሮች መኖሩን ያምናሉ፡፡


ከተማ አስተዳደሩ አሁን ላይ ወንዞች አካባቢ እየተሰሩ ካሉ ፕሮጀክቶች ጋር በማስተሳሰር ፍሳሽ ቆሻሻ አወጋገድን ሥርዓት እንድይዝ ለማድረግ እየተደረገ ነው ብለዋል፡፡

ማህበረሰቡ ጋር አሁንም ድረስ ቆሻሻ አወጋገድ ላይ ከፍተኛ ችግር አለ ያሉት ዶክተር እሸቱ ከግለሰብ ጀምሮ እስከ ተቋማት ድረስ መንገድ ላይ ቆሻሻ ሲጥሉ ይስተዋላል ሲሉ ይናገራሉ፡፡


እነዚህ አመለካከት ለመቀየር በየጊዜው የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራ እየተሰራ ነው ያሉ ሲሆን ማህበረሰቡም እንዲህ ዓይነት ድርጊቶች ሲከናወኑ ሊያስቆም ይገባል ብለዋል፡፡


የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ባለፈው ዓመት ከ #ኮሪደር_ልማት ጋር በተያያዘ ባወጣው ደንብ መሰረት ቆሻሻ አለአግባብ ሲያስወግድ የተገኘ ግለሰቦችም ሆነ ድርጅቶች እንደየ ጥፋት መጠኑ እስከ 100,000 ብሮች ድረስ እንደሚያስቀጣ ይፋ ማድረጉ ይታወሳል፡፡


ሙሉ ዘገባውን በድምፅ ለማድመጥ ይህንን ማስፈንጠሪያ ይጫኑ… https://tinyurl.com/3dvuj757


በረከት አካሉ

Comments


bottom of page