top of page

ጥቅምት 29፣2016 - ሕብረት ኢንሹራንስ በ2015 በጀት ዓመት የተጣራ 327 ሚሊዮን ብር ማትረፉን ተናገረ።

ኩባንያው በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት ከ1 ቢሊዮን ብር በላይ የአረቦን ገቢ መሰብሰቡንም ጠቅሷል።


ሕብረት ኢንሹራንስ 29ኛ የባለአክሲዮኖች መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ በዛሬው እለት ተካሂዷል፡፡


ኩባንያው በበጀት ዓመቱ ከግብር በፊት ብር 390.7 ሚሊዮን ብር ትርፍ ማስበዝገቡ የተነገረ ሲሆን ይህም ካምናው ተማሳሳይ ወቅት ጋር ሲመሳከር የ89 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል፡፡


ሕብረት ኢንሹራንስ በ2015 በጀት ዓመት ከግብር በኋላ ያገኘው የተጣራ ትርፍ አምና ከተገኘው ጋር ሲነፃፀር የ80 በመቶ ጭማሪ ማሳየቱን የኩባንያው የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ አቶ ወንድወሰን ተሾመ ተናግረዋል፡፡


የንግድ እንቅስቃሴዎች መቀዛቀዝ፣ የውጭ ምንዛሪ እጥረት፣ ከፍተኛ የዋጋ ግሽበት ካጋጠሙ በርካታ ችግሮች መካከል ናቸው ሲሉ የቦርድ ሰብሳቢው አስረድተዋል፡፡


ችግሮች ቢኖሩም የኩባንያው ሃላፊዎች በሰሩት ጠንካራ ስራ ኩባንያንያው የበጀት ዓመቱን እጅግ ስኬታማ በሚባል ውጤት አጠናቋል ተብሏል፡፡


ኩባንያው ሕይወት ነክ ካልሆነው የመድህን ዘርፍ 1.3 ቢሊዮን ብር የአረቦን ገቢ የሰበሰበ ሲሆን በዚህ የመድህን ዘርፍ ለተገኘው ከፍተኛ እድገት በተሽከርካሪ ኢንሹራንስ የሽፋን ዓይነት እ.ኤ.አ. ከኅዳር 2022 ጀምሮ ተግባራዊ ያደረግው የአረቦን ተመን ጭማሪ ዋንኛውን አስተዋፅኦ ማበርከቱ ተጠቅሷል፡፡


ሕብረት ኢንሹራንስ በ2015 በበጀት ዓመቱ በአጠቃላይ በሁሉም የኢንሹራንስ የሽፋን ዓይነቶች ከፍተኛ እድገት አስመዝግቤያሁ ብሏል፡፡


በሕጋዊ ሃላፊነት ኢንሹራንስ ሽፋን የ76 በመቶ፣ በእሳትና በድንገተኛ አደጋ እንዲሁም በአቪዬሽን በእያንዳንዱ የ37 በመቶ፣ በጤናና የጉዳት ኢንሹራንስ 24 በመቶ፣ በገንዘብ ነክ ኢንሹራንስ የ22 በመቶ እድገት ተመዝግቧል ተብሏል፡፡


በበጀት ዓመቱ ከፍተኛው የአረቦን ገቢ የተሰበሰበው ከተሽከርካሪ ኢንሹራንስ ሲሆን ይህም ከአጠቃላዩ የአረቦን ገቢ የ64 በመቶ ድርሻ መያዙን የቦርድ ሰብሳቢው አስረድተዋል፡፡


ኩባንያው በበጀት ዓመቱ የሕይወት ነክ ባልሆነው እና በሕይወት ነክ የመድን ዘርፎች ለካሣ ክፍያ የተከፈለው ወጪ 463.5 ሚሊዮን ብር ነው ብሏል፡፡


ይህም በዋናኝነት እያደገ ከመጣው የኩባንያው የአረቦን ገቢ፣ ከተሸከርካሪ አደጋ መብዛት እና አጠቃላይ የእቃዎች ከፍተኛ የገበያ ዋጋ ጭማሪ ጋር የተያያዘ ነው ሲባል ሰምተናል፡፡


ሕብርት ኢንሹራን የተከፈለ ካፒታሉ በ 68 በመቶ ጨምሮ 840.6 ሚሊዮን ብር መድረሱን ተናግሯል፡፡


ጠቅላላ ሃብቱም 3.29 ቢሊዮን ብር ደርሷል ሲሉ አቶ ውንድወሳን ተሾመ አስረድተዋል፡፡


የኩባንያው ጠቅላላ የባለአክሲዮኖች ብዛትም 704 ደርሷል ተብሏል፡፡


የሸገርንወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ… https://bit.ly/33KMCqz




Comments


bottom of page