የፋሽን ዲዛይነሮችን፣ የጨርቃጨርቅ እና ቆዳ ኢንዱስትሪ ባለቤቶችን ያገናኘው 10ኛው የአፍሪካ ሶርሲንግና ፋሽን ሳምንት በአዲስ አበባ መካሄድ ጀመረ፡፡
ከ30 ሀገራት በላይ የተውጣጡ ከ250 በላይ የፋሽን፣ ጨርቃጨርቅ እና ቆዳ ኢንዱስትሪዎችዎቸን በአንድ ጣራ ስር የሚያሰባስብ መሆኑ ተነግሯል፡፡
የኢንዱስት ሚኒስትሩ መለኩ አለበል፣የቱሪዝም ሚኒስትሯ ሰላማዊት ካሳ እና ሌሎች የከፈቱት ሲሆን እስከ ህዳር 02 ቀን 2017 ዓ.ም ይቆያል።
ዝግጅቱ አለም አቀፍ ብራንዶችን፣ የኢንዱስትሪ መሪዎችን እና ፈጣሪዎችን በአንድ ጣሪያ ስር በማሰብሰብ እስካሁን ከተደረጉት ዝግጅቶች ሁሉ ትልቁ ያደርገዋል ሲባል ሰምተናል፡፡
የአፍሪካ ሶርሲንግና ፋሽን ሳምንት ከተመሠረተበት ጊዜ ጀምሮ በጨርቃ ጨርቅ፣ በአልባሳት እና የቆዳ እሴት ሰንሰለቶች መካከል ትብብርን በማጎልበት እና ንግድን በማመቻቸት በአህጉሪቱ ትልቁ የፋሽን መድርክ ሆኖ ቆይቷል ተብሏል፡፡
ዛሬ በተከፈተው እና ለመጪዎቹ አራት ቀናት በሚቆየው የፋሽን ፣ጨርቃጨርቅ እና ቆዳ ኢንዱስትሪዎችን በአንድ ጣራ ስር ያሰባሰበው ዝግጅት ከ30 ሀገራት በላይ የተውጣጡ ከ250 በላይ የዘርፉ ተዋኒያኖች ኤግዚቢሽኖችን ያሳያሉ ፡፡
ከ60 በላይ ሀገራት የሚመጡ ከ7,000 በላይ የንግድ አቀለጣጣፊዎችም ይታደማሉ፡፡
ይህም ለጎብኚዎች አና ተሳታፊዎች በፋሽን ኢንደስትሪ ዘርፍ አለሚቱ የደረሰችበትን ድረጃ አንዲገነዘቡ፣ ፈጠራዎች የት አንደደረሱ አጠቃላይ እይታ ይሰጣል ሲሉ አዘጋጆቹ አስረድተዋል።
ተሳታፊዎች አና ጎብኚዎች ወቅታዊውን የጨርቃጨርቅ፣ሌዘር እና ፋሽን ኢንዱስትሪ በተመለከተ በኮንፈረንሶች እና የፓናል ውይይቶች ላይ ለመሳተፍ እድል ያገኛሉ ሲባልም ሰምተናል።
ዝግጅቱ ኤግዚቢሽንን ያካተተ ሲሆን በዚህ ኤግዚቢሽን በጨርቃ ጨርቅ፣ ፋሽን እና ቆዳ ማምረት በተለይም በዘላቂ አሠራሮች ላይ ያተኮሩ የቅርብ ጊዜ እድገቶችን ይታዩበታል ተብሏል፡፡
ከመላው አፍሪካ የተውጣጡ ምርጥ ዲዛይነሮች ስራ የሚታይበት የፋሽን ዘግጅት በነገው እለት አንደሚቀርብም አዘጋጆቹ ተናግረዋል፡፡
የአፍሪካ ሶርሲንግ እና ፋሽን ሳምንት በአህጉረ አፍሪካ በፋሽን፣ በዘላቂነት እና በፈጠራ ቀዳሚው ስብሰባ ነው።
ታዋቂ ዓለም አቀፍ ገዢዎችን፣ ባለ መዋዕለነዋዮችን፣ ብራንዶችን እና የችርቻሮ ንግድ መሪዎችን ከአፍሪካ ቀዳሚ ፋሽን እና አምራች ዘርፍ ተዋናዮች የሚገናኙበት ነው፡፡
ፋሲካ ሙሉወርቅ
Kommentarer