በሐይቆች እና ግድቦች ከመሰራጨቱ ባለፈ በህዳሴ ግድብም ላይ ተከስቷል የተባለው የእምቦጭ አረም ከፍተኛ አደጋን እንደደቀነ የዘርፉ ተመራማሪዎች እያስጠነቀቁ ነው፡፡
የውሃ አካላትን ሙሉ በሙሉ በማጥፋት ወደ የብስነት ሊቀይራቸው እንደሚችል የተነገረለትን የእምቦጭ አረም ለማጥፋት ደግሞ ምርምር ካደረጉ ዩኒቨርስቲዎች መካከል አንዱ የሆነው የባህር ዳር ዩኒቨርስቲ ምርምሬ ውጤት የታየበት ነው ይላል፡፡
ከእምቦጭ ተፈጥራዊ ማዳበሪያን ማምረት፣ ነቀዞችን በአረሙ ላይ በመልቀቅ ምግባታቸው እንዲያደርጉት ማድረግ እና አረሙን ወደ ባዩ ጋዝ በመቀየር የሀይል ምንጭ ማድረግ የዩኒቨርስቲው የምርምር ውጤቶች ናቸው፡፡
ታዲያ ለምን ጥናቱን ስራ ላይ አውሎ እንደ ጣና ያሉ ሐይቆችወን እየተስፋፋ ካለው አረም መታደግ አልተቻለም፡፡
ምንታምር ፀጋው
Comments