top of page

ጥቅምት 30፣2016 -ኢትዮቴሌኮም በበጎ ሥራ ለተሰማሩ ድርጅቶች ገቢ የሚያገኙበትን የድጋፍ መንገድ ነደፈላቸው

ኢትዮቴሌኮም ከህዳር ወር ጀምሮ እሰከ ሰኔ 2016 ዓ.ም ድረስ ለ8 ወር በበጎ ሥራለተሰማሩ ድርጅቶች ገቢ የሚያገኙበትን የድጋፍ መንገድ ነደፈላቸው።


የተመረጡትድርጅቶቹ 8 መሆናቸውን ሰምተናል።


እያንዳንዱ ወር በበጎ ሥራ በተሰማሩ ድርጅቶች ስም ይሰየማል ተብሏል።


በዚህበተነደፈው ፕሮግራም ለ8 ወር የበጎ አስተዋፆ የገቢ ማሰባሰቢያ ሥራ በብርቱ ይሠራል ተብሏል።


ስምንቱንወራቶች በበጎ አድራጎቱ ድርጅት ስም በመሰየም ከወትሮው በተለየ መንገድ የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም እንደሚኖር ኩባንያው ተናግሯል።


በዚሁ ፕሮግራም የሀገር ሰዎች በኩባንያው ማህበራዊ ትስስር ገፆች ላይ በሚያደርጉት ዘመቻ ወይም አዲስ ደንበኝነት ብዛት ልክ ገቢ ለመሰብሰብ የተቀረፀ ፕሮግራም ነው ተብሏል።


በተጨመሪም ኢትዮ ቴሌኮምለነዚህ በጎ አድራጊዎች በሰጣቸው አጭር ቁጥር እና የቴሌብር ቁጥሮች የገቢ ማሰባሰቢያ በዘመቻው ጊዜ ውስጥ የሚሰበሰበው ገንዘብ ላይ ኩባንያው የራሱን ድጋፍ ጨምሮ ለሰብአዊ ዓላማ እንዲውል ታስቧል።


በዚህ የማህበራዊ ትስስር ገፆች ተሳትፎ እና ገቢ የማሰባሰብ ዘመቻ የበጎ አድራጎት ድርጅቶች እና አብረዋቸው የሚሰሩ ታዋቂ ሰዎች ይሳተፉበታል ተብሏል።


‘’ዘላቂየጋራ ማህበራዊ ሀላፊነት ለወገን ብሩህ ተስፋ’’ በተሰኘው የድጋፍ ማሰባሰቢያ ዘመቻ የልብ ህሙማን ህፃናት መርጃ ማዕከል፣ ጌርጌሴኖን የአእምሮ ህሙማን መርጃ ፣ኢትዮጵያ ካንሰር አሶሴሽን፣ የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር፣ ሙዳይ በጎ አድራጎት፣ መቄዶኒያ አረጋዊ መርጃ፣ ሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ እና ኸይር በጎ አድራጎት ድርጅቶችን አካቷል፡፡


ተህቦ ንጉሴ

የሸገርንወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ… https://bit.ly/33KMCqz

Comentários


bottom of page