‘’ኢትዮጵያ ትናንት አለም አቀፍ ህግ ሆኖ ተፈፃሚ መሆን ለመጀመረው ለናይል ተፋሰስ የትብብር የህግ ማዕቀፍ እውን መሆን ከየትኛውም የተፋሰሱ ሀገራት በላይ ከፍተኛ አስተዋፅኦ አድርጋለች፡፡’’
ይህን ያሉት የውሃ እና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ኢንጂነር ሀብታሙ ኢተፋ ናቸው፡፡
ሚኒስትሩ ዛሬ በመስሪያ ቤታቸው ለጋዜጠኞች ከ15 ዓመት በላይ ፈጅቶ በትላንትናው እለት ህጋዊ እውቅና ስላገኘው የትብብር ማዕቀፍ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡
ኢትዮጵያ ስምምነቱ እውን እንዲሆን ከፍተኛ ጥረት ማድረጓ የተናገሩት ሚኒስትሩ ለዚህም ቀድሞ የነበረው ስምምነት የላይኛውን የተፋሰሱ አገራት ያገለለ በመሆኑ ነው ብለዋል፡፡
ስምምነቱ በሶስት ክፍል 15 ዋና ዋና መርሆች አሉት ብለዋል፡፡
በመጀመሪያው ክፍል ውሃውን በፍትሃዊነት ከመጠቀም መብት ጋር የሚያያዙ ጉዳዮች የያዘ መሆኑን የውሃ እና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ኢንጂነር ሀብታሙ ኢተፋ ተናግረዋል፡፡
የውሃ ሀብቱን መጠቀም፣ መንከባከብ፣ እና በተፋሰሱ ላይ የልማት ስራዎችን የመከናወን ሀላፊነቱን ለሁሉም ተፋሰስ አገራት የሚሰጥ እና በህጉ እንዲገዙ የሚያስገድዱ ሥርዓቶችን የያዘ መሆኑን ኢንጂነር ሀብታሙ አስረድተዋል፡፡
በሶስተኛ ደረጃ ደግሞ መረጃ መለዋወጥን የያዘ ነው የተባለ ሲሆን ይህ ማለትም የልማት እቅዶችን፣ የውሃ ፍሰት መጠንን እና ሌሎች ጉዳዮችን የያዘ መሆኑን ሚኒስትሩ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ጠቁሟል፡፡
የትብብር ማዕቀፍ ስምምነቱ 45 አንቀፆች አሉት የተባለ ሲሆን ከዚህ ውስት 30 የሚሆነው አንቀፅ ከህግና ተቋም ጋር የሚያያዝ መሆኑን ኢንጅነር ሀብታሙ ይተፋ ተናግረዋል፡፡
የትብብር ማዕቀፉ ከዚህ በፊት የነበሩ አሳሪ ህጎችን ያስቀረ ሁሉም የተፋሰሱ ሀገራት ውሃውን እኩል መጠቀም የሚችሉበትን መብት የሚሰጥ ነው ተብሎለታል፡፡
ከዚህ በፊት የነበረው ስምምነት የላይኛውን የተፋሰሱ አገራት ያገለለ እንደነበረ የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ኢንጂነር ሀብታሙ ኢተፋ አስረድተዋል፡፡
የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትሩ አብታሙ ይተፋ በ6 ወር ውስጥ የትብብር ስምምነቱን የሚያስተባብር አፅዳቂ አገራት በውሀው ላይ የሚሰሩትን ስራዎችን የሚደግፈው ኮሚሽን በ6 ወር ውስጥ ይቋቋማል ተብሏል፡፡
ይህ በትናንትናው ዕለት ህጋዊ እውቅና ያገኘው ስምምነት እውን እንዲሆን የድርሻቸውን ለተወጡ መሪዎች የስራ ሀላፊዎች እና ባለሙያዎች ሚኒስትሩ ምስጋና አቅበዋል፡፡
ያሬድ እንዳሻው
Comments