top of page

ጥቅምት 5፣2017 - ለመሆኑ በኢትዮጵያ የሚታረቀው ማን ከማን ጋር ነው? እንዴትስ?

በኢትዮጵያ በተለያዩ ማህበረሰቦች ዘንድ የጋራ መግባባት ላይ ያልተደረሰባቸው ጉዳዮች እንዳሉ ተደጋግሞ ሲነገር ይሰማል፡፡


በአብዛኛው መነሻቸው ያለፉት ዓመታት ክስተቶች እንደሆኑ የሚነገርላቸው፤ እነዚህ አለመግባባቶች በብዙዎች ዘንድ ቁረሾ እያኖሩ እንደዘለቁ ይነገራል፡፡


በሂደት ላይ የሚገኙት እንደ የሽግግር ፍትህ እና የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን፤ ያሉትን አለመግባባቶች እና በደሎችን ለመፍታት ታሳቢ ተደርገው መጀመራቸውን ይነገራል፡፡


በየጊዜውና በየቦታው ለሚፈጠሩ አለመግባባቶች መነሻቸው ‘’ፖለቲከኞች ዋነኞቹ ናቸው’’ የሚሉ እንዳሉ ሁሉ ‘’ምሁራንና የማህበረሰብ አንቂ’’ የሚባሉትን ተጠያቂ የሚያደርጉ እንዲሁም ሎሎችም የሚጠቅሱ አሉ፡፡


መነሻቸው ምንም ሆነ ምን፤ በአሁን ወቅት አለመግባባቶቹ ተፈትተው፣ ሰላም ሰፍኖ በበጎ በማይተያዩት መካከል እርቅ ማውረድ እንደሚያስፈልግ ብዙዎች የሚስማሙበት ነው፡፡


ይህ እንዴት ይቻላል ሲል ሸገር ኤፍ ኤም ራዲዮ ጋረደው አሰፋን(ዶ/ር) ጠይቋቸዋል፡፡


ዶ/ር ጋረደው በሰላም፣ በእርቅ እና በግጭት አፈታት ባለሞያነት እንዲሁም ተያያዥ ጉዳዮች ላይ ጥናቶችን በማድረግ ከ15 ዓመታት በላይ ሰርተዋል፡፡


ባለሞያው እንደሚሉት ከሆነ በኢትዮጵያ ያለፉት ዓመታት ቁርሾዎች ለአሁኖቹ አለመግባባቶች መነሻ ሆነው ችግር እያስከተሉ በመሆኑ እርቅ ያስፈልጋል፡፡


ለመሆኑ በኢትዮጵያ የሚታረቀው ማን ከማን ጋር ነው?


በሀገሪቱ አልግባባ ያሉትን አካላት ለማስታረቅ በተለያዩ መንገዶች ሲሞከር በቆይም፤ አለመግባባቶቹ ዛሬም ድረስ ቀጥለው ሞትና ጉዳት እያስከተሉ እንደሆነ ይታያል፡፡


ከሙከራዎቹ አንዱ የነበረው የእርቀ ሰላም ኮሚሽንም የታለመለት አላማ ሳይመታ ከስሞ፣ ቢሮው ለሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ማስረከቡ ይታወቃል፡፡


ታዲያ እንደ ዶ/ር ጋረደው ያሉ ባለሞያዎች ያስፈልጋል የሚሉት እርቅ፤ እንደቀደሙት ሙከራዎች ሳይሳካ እንዳይቀር በማንና እንዴትስ ነው መመራት ያለበት?



ማንያዘዋል ጌታሁን ያሰናዳውን በምንታምር ጸጋው

Comments


bottom of page