top of page

ጥቅምት 5፣2017 - ''የውስጥ ገቢዬን ለማሳደግ በብርቱ እየሰራሁ ነው'' ሲል የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ገቢዎች ቢሮ ተናገረ

የበጀት እጥረት እንዳይገጥመኝ የውስጥ ገቢዬን ለማሳደግ በብርቱ እየሰራሁ ነው ሲል ከተመሰረተ አንድ ዓመቱን የያዘው የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ተናግሯል፡፡


ክልሉ 2017 በጀት ዓመት 20 ቢሊዮን ብር ለመሰብሰብ አቅጄ እየሰራሁነ ነው ብሏል፡፡


ግብር በመሰብሰብ ሂደት የሚገጥሙኝ ችግሮችንም በተቻለኝ ሁሉ መላ እየዘየድኩላቸው ነው ብሏል፡፡


ክልሉ ባለፈው ዓመት ገጥመውኛል ካላቸው ችግሮች መካከል #የሰራተኞች_ስነ_ምግባር ጉድለት አንዱ ነው፡፡


የተጣለባቸውን ሀላፊነት ችላ ብለው ከነጋዴው ጋር በመሰባጠር ህገወጥ ተግባራት ላይ የሚሰማሩ ሰራተኞቼን ከእንግዲህ አልታገስምም ብሏል፡፡


በሀገር ዓቀፍ እና በክልሉ በገቢ መስሪያ ቤቶች የሚሰሩ የስነ ምግባር ጉድለት ያለባቸው ሰራተኞች እንዳሉ፤ በተለያየ ጊዜ በተደረጉ ጥናቶች ታይቷል ተብሏል፡፡


ይህም በገቢ አሰባሰብ ላይ አሉታዊ አስተዋጽኦ እየፈጠረ ስለሆነ፤ መሰል ችግር የሚታይባቸው ሰራተኞቼን ጠንከር ያለ እርምጃ ለመውሰድ እየተሰናዳሁ ነው ሲል የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል አስረድቷል፡፡


ክልሉ ከዚህ በፊት በእንዲህ አይነት ተግባር ተሰማርተው በተገኙት ላይ፤ ቀላል ማስጠንቀቂያ ከመስጠት እስከ ደረጃ ዝቅ ማድረግ እንዲሁም ከስራ የማሰናበት እርምጃ ሲወስድ እንደቆየ ተጠቅሷል፡፡


በዚህ በጀት ዓመትም የህግ ማስከበር እርምጃን አጠናክሮ እንደሚወስድ ተናግሯል፡፡

ይህንን ለሸገር የነገሩት፤ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ገቢዎች ቢሮ የትምህርት እና የኮሙኒኬሽን ዳይሮክቶሬት ዳይሬክተር ወ/ሮ ህይወት ከላይ ናቸው፡፡


ለተደረጉ ግብይቶች #ደረሰኝ በመቁረጥ ረገድ የሚታየው ከፍተኛ ክፍተት፤ በገቢ አሰበሰብ ሂደት የሚገጥም ሌላኛው ችግር እንደሆነ ወ/ሮ ህይወት ነግረውናል፡፡


ይህንን ችግር ለመፍታት ለህብረተሰቡ ያለደረሰኝ እንዳይገበያይ ግንዛቤ እየሰጠን ነው ያሉ ሲሆን፤ የተለያዩ ቴክኖሎጂዎችን ከግብር ስርዓት ጋር በማስተዋወቅም ገቢ ለመሰብሰብ እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡


ክልሉ በተጨማሪም፤ የገጠር መሬት መጠቀሚያ ክፍያ እና የግብርና ሥራ ገቢ ግብር ከዚህ ቀደም በተሻለ በመሰብሰብ የበጀት ጉድለቶች እንዳይታዩ እንደሚጥር ተናግሯል፡፡


ሙሉ ዘገባውን በድምፅ ለማድመጥ ይህንን ይጫኑ..



ማንያዘዋል ጌታሁን

Commentaires


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page