top of page

ጥቅምት 6፣2017 - ትናንት ብሔራዊ ባንክ አዲስ መምሪያ ለባንኮች አስተላልፏል፡፡

ትናንት ብሔራዊ ባንክ አዲስ መምሪያ ለባንኮች አስተላልፏል፡፡


የውጭ ምንዛሪ አስተዳደርን የተመለከተው እና በባንኩ መግለጫ የተካተተው ይዘት ከዚህ ቀደም ብሔራዊ ባንክ ለባንኮች ያስተላለፈውን መመሪያ የሚሽር ነው፡፡


የውጭ ምንዛሪ ሲገዙና ሲሸጡ የኮሚሽን እና ተያያዥ ክፍያዎችን ከመግዣና መሸጫ ዋጋ ነጥለው ለብቻ እንዲያሳውቁ ወይም ከደንበኞቻቸው ጋር እንዲደራደሩ የሚል ይዘት አለው፡፡


አዲሱ መመሪያ በተለይ ለአስመጪ ነጋዴዎች ፋይዳው ምን ሊሆን ይችላል? የሚለውን በተመለከተ የምጣኔ ሐብት ባለሞያውን አቶ ዋሲሁን በላይን ጠይቀናቸዋል፡፡


ባለሞያው አዲሱ የብሔራዊ ባንክ ውሳኔ ለአስመጭዎች ይህ ነው የተባለ ፋይዳ ይኖረዋል ብለው አያምኑም፡፡


ለሰዎች ስነ ልቦና የባንኮች የመግዣና የመሸጫ ዋጋ የቀነሰ መስሎ እንዲታይ ያደርግ ይሆናል እንጂ በስውር ግን ልዩነቱ እንደሰፋ መቀጠሉ አይቀርም ያሉት ባለሞያው ብሔራዊ ባንክ ማድረግ ካለበት ማድረግ የነበረበት ባንኮች ያስከፍሉታል የተባለውን የተጋነነ ኮሚሽን ፈር እንዲይዝ ማድረግ ነበር ሲሉም ነግረውናል፡፡



ትዕግስት ዘሪሁን

留言


bottom of page