top of page

ጥቅምት 7፣2017 - ኢትዮ ቴሌኮም የ30 ቢሊየን ብር አክሰዮን ለህዝብ ሽያጭ ክፍት አደረገ።

ኢትዮ ቴሌኮም የ30 ቢሊየን ብር ወይም የ 10 በመቶ ድርሻውን አክሰዮን ለህዝብ ሽያጭ ክፍት አደረገ።


ይህ ዛሬ የተጀመረው መደበኛ የአክስዮን ሽያጭ የመጀመርያው ምዕራፍ መሆኑን ሰምተናል።


ለካፒታል ገበያ መንገድ የከፈተውና የመጀመርያ የመደበኛ የኢትዮ ቴሌኮምን የ 10 በመቶ ሽያጭ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በይፋ አስጀምረዋል።


የኢትዮ ቴሌኮምን የባለቤትነት ድርሻ ለህዝብ ለማቅረብ 1 ዓመት የጊዜ ማእቀፍ መውሰዱን፤ እንዲሁም በካፒታል ገበያ ና የንግድ ህጉን በጠበቀ መልኩ መከፈቱን  የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈፃሚ ፍሬህይወት ታምሩ ተናግረዋል።


ኢትዮ ቴሌኮም በተገመተ 300 ቢሊየን ብር ሀብቱ አጠቃላይ የሼር ድርሻው የተቆጠረ 1 ቢሊየን እንደሆነ ታውቋል።


ከዚህ ውስጥ ኢትዮ ቴሌኮም በመጀመርያው ምእራፍ በመደበኛ የአክስዮን ሽያጭ 100 ሚሊየን ሼር ለደንበኞቹ ለመሸጥ ወደ ገበያ አውጥቷል።


ይህ 100 ሚሊየን ሼር በገንዘብ ሲሰላ 30 ቢሊየን ብር እንደሚተመን ከደንበኛ ሳቢ መግለጫው ላይ አንብበናል።


የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈፃሚ ፍሬህይወት ታምሩ፤በመጀመሪያው ዙር መደበኛ የአክሲዮን ሽያጭ ከቀረበው 100 ሚሊዮን አክስዮን ውስጥ ዝቅተኛው ሽያጭ 33 ሼር ብቻ መሆኑን እና ከፍተኛው ደግሞ 3ሺ 333 መሆኑን ይፋ አድርገዋል።


ይህም በገንዘብ ሲተመን 33 ሼሩ 9,900 ብር ሲሆን ፤ከፍተኛ ጣሪያው ደግሞ 3,333 ሼር ወይም አክስዮን ደግሞ 999,900 ብር መሆኑ ታውቌል።

ኢትዮ ቴሌኮም በመደበኛ የአክስዮን ገበያ ያቀረበው የአንድ ሼር ዋጋ 300 ብር ሲሆን ይህ ገበያ ከዛሬ ጥቅምት 6፣2017 ዓ.ም ጀምሮ ለ 79 ቀናት ማለትም እስከ ታህሳስ ታህሳስ 25 ድረስ ክፍት እንደሆነ ዋና ስራ አስፈፃሚዋ አስረድተዋል።


በገበያው ሼሩ ቀድሞ ከተጠናቀቀ አክስዮኑ ከተቆረጠለት ቀን ቀድሞ እንደሚዘጋ ታውቌል።


ከመጀመርያው ምእራፍና ከመደበኛው የአክስዮን ሽያጭ መጠናቀቅ በውኃላ

በ ኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ መስፈርት መሰረት ድልድል እንደሚደረግ ታውቋል።


ደንበኞች ይህን አክስዮን ለመግዛት የቴሌ ብር ደንበኛ መሆን እንዳለባቸውና ብሔራዊ የዲጅታል መታወቅያ ወይም ማንነታቸውን በግልፅ የሚያስረዳ መታወቅያ ፤ በዲጅታል ማቅረብ እንደሚኖርባቸው ዋና ስራ አስፈፃሚዋ መክረዋል።


በዚህ ሂደት ውስጥ የኢትዮዽያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ የካፒታል ገበያ ባለስልጣን እና ሌሎችም ተሳትፈዋል።


በመጀመሪያው ዙር የመደበኛ አክሲዮን ሽያጭ ምዕራፍ ዲጅታል ኢትዮጵያን በቅርበት ይዞ ለመጓዝ ፤ ኢትዮ ቴሌኮም የስቶክ ማርኬት ወይም የድርሻ ገበያውን በር ዛሬ በይፋ ከፍቷል ተብሏል።


ኢትዮ ቴሌኮም የ10 በመቶ ድርሻውን ማለትም  የ30 ቢሊየን ብር ወይም የአንድ ሚሊየን ሼሩን ለኢትዮዽያውያን ብቻ እና በ ኢትዮጵያ ብር ብቻ እንደሚሸጥ ተሰምቷል።


ተህቦ ንጉሴ


Comments


bottom of page