ባንኩ እና አየር መንገዱ ዛሬ የተፈራረሙት ስምምነት በኢትዮጵያ የባንክ ኢንዱስትሪ በዓይነቱ የመጀመሪያው መሆኑ ተነግሮለታል፡፡
ይህ ስምምነት የዘመን ባንክን መለያ(ብራንድ) በዓለም አቀፍ ደረጃ ክፍ አድርጎ ለማስተዋወቅ ያስችላል ተብሎለታል፡፡
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በተለየዩ አማራጮቾች በዓመት ከ140 ሚሊዮን በላይ መንገደኞች ጋር እንደሚገኛን የተነገረ ሲሆን እነዚህን መንገደኞች ደግሞ ዘመን ባንክ በቀላሉ እንዲያገኙ እና እራሱን እንዲያስተዋውቅ ስምምነቱ እድል ይፈጥርለታል ተብሏል፡፡
ዘመን ባንክ በበረራ ውስጥ መዝናኛ፣ በኤርፖርት ስክሪን፣ በአቅጣጫ ተቋሚ(ናቪጌተር)፣ በሰላምታ መፅሔቶች የመተዋወቅ እድል በስምነቱ መሰረት ያገኛል ተብሏል።
በዚህ ስምምነት የኢትዮጵያ አየር መንገድ የኢትዮጵያን የፋይናንሺያል ዘርፍን ለአለም አቀፍ የቢዝነስ ምህዳር በማስተዋወቅ ባለሃብቶች በኢትዮጵያ መዋዕለ ነዋያቸውን እንዲያፈሱ የበኩሉን ሚና እንዲጫወት ያስችለዋል።
ይህም የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንትን በማስተዋወቅ በኩል ትልቅ ሚና እንደሚጫወት ተነግረሯል።
የዘመን ባንክ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ደረጀ ዘበነ ዘመን ባንክ በኢትዮጵያ የፋይናንስ ዘርፍ ልዩ አገልግሎቶችንና ምርቶችን በማስተዋወቅ እንደሚታወቅ አስታውሰው የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሚዲያ መድረኮችን መጠቀም ዓለም አቀፍ ደንበኞችን እንዲያገኙ እና የኢትዮጵያ የፋይናንስ ዘርፍ መስታወት ሆኖ እንዲያገለግል ሰምምነቱ ያስችላል ብለዋል፡፡
ዘመን ባንክ አጠቃላይ የተመዘገበ ካፒታሉ 13.7 ቢሊዮን ብር፣ የተከፈለ ካፒታሉ ሕጋዊ መጠባበቂያን ጨምሮ 7.74 ቢሊዮን ብር እንደደረሰለት ተናግሯል።
የባንኩ አጠቃላይ ሀብት ከ50 ቢሊዮን ብር በላይ ደርሷል የተባለ ሲሆን 110 ቅርንጫፎች እና ከ200 በላይ የኤቲኤም ማሽኖች አሉኝ ብሏል፡፡
ንጋቱ ሙሉ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ… https://bit.ly/33KMCqz
Comments