top of page

ጥቅምት 9፣2017 - ዘመን ባንክ በ2016 በጀት ዓመት ያልተጣራ 3.77 ቢሊዮን ብር አተረፍኩ አለ።

  • sheger1021fm
  • Oct 19, 2024
  • 1 min read

ዘመን ባንክ በ2016 በጀት ዓመት ያልተጣራ 3.77 ቢሊዮን ብር አተረፍኩ አለ።


በዚህም በተጠናቀቀው በጀት ዓመት እቅዴን ሙሉ በሙሉ አሳክቻለሁ፣ የተገኘው ትርፍም ካለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸር በ1.01 ቢሊየን ብር ወይም በ36.8 በመቶ ብልጫ አለው ብሏል።


ባንኩ ይህንን ያለው 16ኛ የባለአክስዮኖች መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔውን በዛሬው ዕለት ባካሄደበት ወቅት ነው።

የባንኩን አጠቃላይ ሀብት በ23.9 በመቶ በማሳደግ ወደ 59.2 ቢሊየን ብር አድርሷል የተባለ ሲሆን በተጠናቀቀው በጀት ዓመት መጨረሻ ላይ የደንበኞች ተቀማጭ ገንዘብ ከቀደመው ዓመት በ17.6 በመቶ አድጎ 43.61 ቢሊየን ብር ደርሷል መባሉን ሰምተናል።


በተጨማሪም በበጀት ዓመቱ መጠናቀቂያ ላይ የባንኩ አገልግሎት ሰጭ ቅርንጫፎች 125 መድረሱ የተነገረ ሲሆን የባንኩ የውጭ ምንዛሪ ግኝት 566 ሚሊየን ዶላር ደርሷል ተብሏል።


የዘመን ባንክ የተከፈለ ካፒታል 7.5 ቢሊዮን ብር አድርሷል ይህም ከቀደመው በጀት ዓመት በ2.45 ቢሊዮን ብር ከፍ ያለ ተብሏል።


በአሁኑ ወቅትም አጠቃላይ የባንኩ የተፈረመ ካፒታል 14.97 ቢሊየን ብር መሆኑ ተነግሯል።


ፋሲካ ሙሉወርቅ

留言


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page