top of page

ጳጉሜ 1፣2016 - ‘’አነቃቂ ንግግር’’ በሚል የሚሰጠው ስልጠና ሊፈተሽ እንደሚገባ የማህበራዊ ሳይንስ ባለሞያዎች እየተናገሩ ነው፡፡

‘’አነቃቂ ንግግር’’ በሚል የሚሰጠው ስልጠና ምንነትና ጠቀሜታው ሊፈተሽ እንደሚገባ እና በዚህ ረገድ የቁጥጥር ስርዓት መኖር እንዳለበት የማህበራዊ ሳይንስ ባለሞያዎች እየተናገሩ ነው፡፡


ከቅርብ ጊዜ ወዲህ አንዳንዶች የስልጠና ማዕከል ከፍተው ሌሎች ደግሞ ማህበራዊ ሚዲያን ተጠቅመው አነቃቂ በሚል መልዕክቶችን ሲያስተላልፉ ይሰማል፡፡


‘’እኔ በዚህ መንገድ ሄጄ ተሳክቶልኛል፤ እናንተም እንዲሳካላችሁ በዚህ መንገድ ሂዱ’’ ሲሉ መስማት እተለመደ መጥቷል፡፡


በ’’አነቃቂ ንግግር’’ ስም የሚተላለፉ እነዚህና መሰል መልዕክቶች ስርዓት ሊበጅላቸው ይገባል ተብሏል፡፡


‘’አንዳንዶቹ መልዕክቶች በተጨባጭ መሬት ላይ ያለውን እውነታ የካዱ ከመስራት ይልቅ ሰዎችን ወደ ምኞት ዓለም የሚያስገቡ፣በአቋራጭ መንገድ ተጠቅመው የሚፈልጉበት መድረስን የሚያበረታቱ’’ መሆናቸውን እንዳስተዋሉ የማህበረሰብ ጥናት ባለሙያና አማካሪው አቶ ቴዎድሮስ አዱኛ ነግረውናል፡፡


በተጨማሪም እነዚህ አነቃቂዎች ‘’ሰዎች ለዘመናት ከኖሩበት እሳቤ ወጥተው አፈንጋጭ እንዲሆኑ የሚያደርጉ፣ የስኬት መንገድ አነቃቂዎቹ የሚሉት ብቻ እንደሆነ አድርገው የሚያስተምሩ’’ መሆናቸው እንዳሳሰባቸው አማካሪው አቶ ቴዎድሮስ ያስረዳሉ፡፡


በዚህ መንገድ የሚተላለፉ መልዕክቶች እየበረከቱ እና በአብዛኛው ከተሞች አካባቢ ያለው ማህበረሰብ እየተከተላቸው በመሆኑ የሚሰጡት ስልጠናም ይሁን ትምህርት ምንነቱ ታውቆ በመንግስት ቁጥጥር እንዲደረግበትም ጠይቀዋል፡፡


የማህበረሰቡን መስተጋብር የሚያላሉ በደመነ ነፍስ የሚነገሩ አነቃቂ ንግግሮች እንዳሉ ሁሉ የሰዎች ህይወት ላይ ትርጉም ያለው ለውጥ የሚያመጡ እንዳሉም እንዳይዘነጋ ተብሏል፡፡



ምንታምር ፀጋው


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…


Telegram: https://shorturl.at/b9p8z


Website: https://shorturl.at/yCz7q


YouTube: https://t.ly/9uH-g


Comments


bottom of page